ኢዮብ 34:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የድሀውን ልቅሶ እስኪሰማ ድረስ፥ የችግረኛውን ድምፅ እስኪሰማ ድረስ፥ እርሱን ከመከተል ርቀዋልና፥ ከመንገዱም አንዱንም አልተመለከቱምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፤ መንገዱንም ችላ ብለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የሚያደርግባቸው፥ እርሱን መከተል ስለ ተዉና ትእዛዞቹንም ስለ ናቁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ሕግ ፈቀቅ ያሉ፥ ፍርዱን አያውቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የድሀውን ልቅሶ ወደ እርሱ ያደርሱ ዘንድ፥ እርሱም የችግረኛውን ድምፅ ይሰማ ዘንድ፥ እርሱን ከመከተል ፈቀቅ ብለዋልና፥ ከመንገዱም ሁሉ አንዱን አልተመለከቱምና። |
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፤ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፤ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና።
“እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና፥ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ።” ሳሙኤልም እጅግ ተቆጥቶ፥ ሌሊቱን ሁሉ ወደ ጌታ ጮኸ።