ኢዮብ 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፤ እንደ አካሄዱም ይከፍለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፤ በአካሄዱም መጠን የሚገባውን ያደርግለታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይመልስለታል፥ ሰውንም እንደ መንገዱ ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰው ሥራውን ይመልስለታል፥ ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል። |
እነሆ፥ ይህን አላውቀውም ብትል፥ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ ሁሉ እንደ ሥራው አይመልስለትምን?
በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፍንም ቢወስድ፥ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፤ እነዚህን ርኩሰቶች ሁሉ አድርጎአልና በእርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በላዩ ላይ ይሆናል።
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።