ኢዮብ 33:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድ፥ ሰውንም ከትዕቢት ይቆጥበው ዘንድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ ከትዕቢት ይጠብቃል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ሰዎች ኃጢአት ከመሥራት እንዲቈጠቡ ያደርጋል፤ ትዕቢትንም ከእነርሱ ያስወግዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውን ከኀጢአቱ ይመልሰው ዘንድ፥ ሥጋውንም ከውድቀት ያድነው ዘንድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድ፥ ከሰውም ትዕቢትን ይሰውር ዘንድ፥ |
እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፥ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውኩህም።
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።