ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ፥ ከንፈሮቼን ከፍቼ እመልሳለሁ።
ተናግሬ መተንፈስ አለብኝ፤ አፌንም ከፍቼ መልስ መስጠት ይገባኛል።
ተናግሬ ይውጣልኝ፤ በአንደበቴ መልስ መስጠት አለብኝ።
ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ። ከንፈሬንም ገልጬ እመልሳለሁ።
ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ፥ ከንፈሬን ገልጬ እመልሳለሁ።
“ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥ የፈለገ ነገር ይምጣብኝ።
ከእኔስ ጋር የሚፋረድ ማን ነው? አሁን እኔ ዝም ብል እሞታለሁ።
“እንድመልስ ሐሳቤ ይገፋፋኝል፥ ስለዚህም ውስጤ መታገሥ አቅቶታል።
እናገር ዘንድ ተውኝ፥ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
እነሆ፥ አንጀቴ በአዲስ ወይን ጠጅ ተሞልቶ ሊቀደድ እንደ ቀረበ አቁማዳ፥ መውጫም እንደሚፈልግ ወይን ጠጅ ሆነ።
በማንም ሰው ፊት ግን አላደላም፥ ማንንም አላቈላምጥም።
“አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር ትቀየማለህን? ቃልንስ ከመናገር ማን ሊቀር ይችላል?