ኢዮብ 31:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፥ የሚበቅለውም ሁሉ ይነቀል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዘራሁትን ሌላ ይብላው፤ ሰብሌም ተነቅሎ ይጥፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የዘራሁትን ሌላ ሰው ይብላው፤ ቡቃያዬም ሁሉ ተነቃቅሎ ይጥፋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፤ በምድር ላይ ሥሬ ይነቀል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፥ የሚበቅለውም ሁሉ ይነቀል። |
እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬና የምድርህን ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ የእህል፥ የወይን ወይም የዘይት፥ የከብትህን ጥጃ ወይም የበግና ፍየል መንጋህን አይተውልህም።
“የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤