ኢዮብ 31:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማን ነው ከአንጀቱ ያልባረከኝ፥ በበጎቼም ጠጉር ያልሞቀ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበጎቼ ጠጕር ስላሞቅሁት፣ ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበጎቼ ጠጒር የተሠራ ልብስ አልብሼው ሞቆት ሳይመርቀኝ የቀረበት ጊዜ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሆች አልመረቁኝ እንደ ሆነ፥ በበጎቼም ጠጕር ትከሻቸው አልሞቀ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐንና ጐኑ ያልባረከችኝ፥ በበጎቼም ጠጕር ያልሞቀ እንደ ሆነ፥ |
እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሓይ ሳትጠልቅ መልስለት። ከዚያም ያመሰግንሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔር ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርልሃል።