ኢዮብ 30:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ባልንጀራ ሆንሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀበሮች ወንድም፣ የጕጕቶችም ባልንጀራ ሆኛለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰው ተለይቼ ለቀበሮ ወንድም ለሰጎንም ባልንጀራ ሆንኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሌሊት ዎፍ ወንድም፥ ለሰጎንም ባልንጀራ ሆንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ባልንጀራ ሆንሁ። |
እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጉረመረምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ላይ በማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።
በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፥ ዋይ ዋይ እላለሁ፥ ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፥ እንደ ሰጎን ልጆችም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ።