ኢዮብ 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ሁሉ ዕድል ፈንታ ለሆነው ለሞት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ ዐውቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞት እንደሚያጠፋኝ አውቃለሁና ለሟችም ሁሉ ማደሪያው ምድር ናትና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሞት ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና። |
እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።
“እነሆም፥ ዛሬ የምድርን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ፤ እናንተም ጌታ ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፤ ሁሉም ነገር ተከነናውኖላችኋል፤ ከእርሱም አንድም የቀረ ነገር የለም።