ከሕመሜ ብርታት የተነሣ ልብሴ ተበላሸ፥ እንደ ቀሚስ ክሳድ ያንቀኛል።
አምላክ በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዷል፤ በልብሴም ክሳድ ዐንቆ ይዞኛል።
ከሕመሜ ጽናት የተነሣ ልብሴ ተቈራፍዶ ተበላሽቶአል፤ እንደ ሸሚዝ ክሳድ አንቆ ይዞኛል።
ከታላቁ ደዌ ኀይል የተነሣ ልብሴ ተበላሸች፤ የልብሴ ክሳድ አነቀችኝ፥ ቀሚሴም በአንገቴ ተጣበቀ።
ከታላቁ ደዌ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተበላሸች፥ እንደ ቀሚስ ክሳድ አነቀችኝ።
አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
ሰይጣንም ከጌታ ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ መርገጫ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው።
ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥ ቆዳዬ ያፈከፍካል እንደገናም ይመግላል።
ዐመፃዎቼ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብለዋልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብደዋልና።
ዓይነ ስውር፥ ወይም የሚያነክስ፥ ወይም የፊቱ ቅርጽ የተበላሸ፥ ወይም ትርፍ አካል ያለው፥