ኢዮብ 30:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋጤ በላዬ ተመለሰብኝ፥ ክብሬንም እንደ ነፋስ ያሳድዱታል፥ ብልጽግናዬም እንደ ደመና አልፋለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድንጋጤ ተውጫለሁ፤ ክብሬ በነፋስ እንደሚወሰድ ተወስዷል፤ በሰላም መኖሬም እንደ ደመና እልም ብሎ ጠፍቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታላቅ ድንጋጤ ይዞኛል፤ ክብሬ እንደ ነፋስ ሽውታ አልፎአል፤ የመዳኔም ተስፋ እንደ ጉም በኖ ጠፍቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋጤ በላዬ ተመላለሰችብኝ፥ ነፍሴ ከእኔ ላይ እለይ እለይ አለች፥ ደኅንነቴም እንደ ተበተነ ደመና አለፈች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋጤ በላዬ ተመለሰችብኝ፥ ክብሬንም እንደ ነፋስ ያሳድዱአታል፥ ደኅንነቴም እንደ ደመና አልፋለች። |
ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋትም እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፍስም ከአውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።