La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል፤ የደነገጥሁበትም ነገር ደርሶብኛል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የተ​ጠ​ራ​ጠ​ር​ሁት ነገር መጥ​ቶ​ብ​ኛ​ልና፥ ያሰ​ብ​ሁ​ትም ደር​ሶ​ብ​ኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።

Ver Capítulo



ኢዮብ 3:25
6 Referencias Cruzadas  

የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።


ድንጋጤ በላዬ ተመለሰብኝ፥ ክብሬንም እንደ ነፋስ ያሳድዱታል፥ ብልጽግናዬም እንደ ደመና አልፋለች።”


ነገር ግን በጎነትን ስጠባበቅ ክፉ ነገር መጣብኝ፥ ብርሃንን ተስፋ ሳደርግ ጨለማ መጣ።


የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም።”


ንጹሕ እንደማታደርገኝ እኔ አውቃለሁና ከመከራዬ ሁሉ የተነሣ እፈራለሁ።


ሰይፍን ፈርታችኋል፥ እኔም ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።