Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 1:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የግብዣው ጊዜ ካለፈ በኋላ ኢዮብ ልኮ ያስመጣቸውና፣ “ምናልባት ልጆቼ ኀጢአት ሠርተው፣ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” በማለት ጧት በማለዳ ስለ እያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ ያነጻቸው ነበር፤ ኢዮብ ይህን ዘወትር ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የግብዣዎቹ ቀኖች ከተፈጸሙ በኋላ ኢዮብ በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹን ያስጠራና በእያንዳንዱ ልጁ ስም መሥዋዕት ያቀርብ ነበር፤ ይህንንም የሚያደርገው “ምናልባት ከልጆቼ አንዱ እግዚአብሔርን በመስደብ በድሎ ይሆናል!” በሚል ስጋት ልጆቹን ከኃጢአት ለማንጻት ነበር። ኢዮብ ይህን ሥርዓት ሳያቋርጥ ዘወትር ይፈጽም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የግ​ብ​ዣ​ውም ቀኖች በተ​ፈ​ጸሙ ጊዜ ኢዮብ ይል​ክና ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ነበር፤ በማ​ለ​ዳም ገሥ​ግሦ፦ ስለ ልጆቹ በቍ​ጥ​ራ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ አንድ ወይ​ፈን ስለ ነፍ​ሳ​ቸው የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርብ ነበር፤ ኢዮብ፥ “ምና​ል​ባት ልጆቼ በል​ባ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ክፉ ነገር ያስቡ ይሆ​ናል” ይል ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 1:5
36 Referencias Cruzadas  

አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፥ አገልጋዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ጥፋታችሁ እንዳላደርግባችሁ ጸሎቱን እሰማለሁ፥ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።”


ኖኅም ለጌታ መሠውያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዓይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።


ልጆችህ በድለውት እንደሆነ፥ እርሱ በበደላቸው እጅ ጥሎአቸዋል።


ሳሙኤልም፥ “አዎን፤ ለሰላም ነው፤ የመጣሁትም ለጌታ መሥዋዕት ላቀርብ ነው፤ እናንተም ራሳችሁን ቀድሳችሁ ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ” ሲል መለሰላቸው። ከዚያም እሴይንና ልጆቹን ቀደሳቸው፤ ወደ መሥዋዕቱም እንዲመጡ ጠራቸው።


በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ እስከ መጨረሻው በጽናት ትጉ።


እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፤ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤


እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”


የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት።


በማግስቱም ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕት የሚሆን ዕንጨትን ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፥ ከእርሱም ጋር ሁለቱን አገልጋዮቹን እና ልጁን ይስሕቅን ይዞ፥ እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ተነሥቶ ጉዞ ጀመረ።


ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


በዚያን ጊዜ ጳውሎስ ሰዎችን ይዞ በማግሥቱ ከእነርሱ ጋር እየነጻ፥ መንጻታቸውን የሚፈጽሙበትን ቀን አስታውቆ ወደ መቅደስ ገባ። በዚያም ቀን ስለ እያንዳንዳቸው መሥዋዕትን አቀረቡ።


እግዚአብሔር ታዲያ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ፥ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?


የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።


በዘመናችን ሁሉ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን።


ኢየሩሳሌም ሆይ! እንድትድኚ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


የጩኸቴን ድምፅ አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።


ያለ ፍርሃት የተፈጠረ፥ እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።


ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?


ሚስቱም፦ “እስከ አሁን ፍጹምነትህን ይዘሃልን? እግዚአብሔርን ስደብና ሙት” አለችው።


ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡን፥ በሮቹንና ቅጥሩንም አነጹ።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገን ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤


የሙሴ አማት ይትሮም የሚቃጠል ቊርባንና መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሊመገቡ ከሙሴ አማት ጋር መጡ።


ጌታም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ።


እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር ቅንዐት እቀናላችኋለሁና።


ጌታ ከዚያ በፊት “እስራኤል” ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ በተወለዱት በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ወሰደ።


የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለጌታም የሰላም መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤል ልጆች ወጣቶችን ላከ።


ወንዶች ልጆቹም ሄደው በየተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያሰናዱ ነበር፥ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ልከው ይጠሩአቸው ነበር።


“ቸርነትን ለወዳጁ የሚነፍግ፥ ሁሉን ቻይ አምላክን መፍራት የተወ ነው።


ኖኅ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ በውስጧ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios