ኢዮብ 3:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትካዜ ምግብ ሆኖኛልና፤ የሥቃይ ጩኸቴም እንደ ውሃ ይፈስሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምግብ ፈንታ እቃትታለሁ፤ ጩኸቴም እንደ ፈሳሽ ውሃ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአዝመራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ስለ ደረሰብኝም አስፈሪ ነገር ሁልጊዜ አለቅሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል። |
ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትህን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር እርሱ ግን የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።
እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።