ኢዮብ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፥ አገልጋይም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በአንድነት ይገኛሉ፤ ባሪያዎችም በዚያ ከጌቶቻቸው ነጻ ይወጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታናሹና ታላቁ በዚያ አሉ፤ ጌታውን ያገለገለ ባሪያም በዚያ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፥ ባሪያም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል። |
ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።