ኢዮብ 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም እንደ ተደበቀበ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፣ ብርሃንም እንዳላየ ሕፃን በሆንሁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይስ ለምን በመሬት ውስጥ እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ የቀንን ብርሃን ፈጽሞ እንዳላየ ሕፃን አልሆንኩም? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም ከእናቱ ማኅፀን እንደ ወጣ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር። |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።