ኢዮብ 29:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለድሀው አባት ነበርሁ፥ ለማላውቀውም ሰው ጠበቃ ነበርሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለድኾች አባት፣ ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለድሃዎች አባት ነበርሁ፥ የማላውቀውንም ሰው ክርክር መረመርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለድሀው አባት ነበርሁ፥ የማላውቀውንም ሰው ሙግት መረመርሁ። |
መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”