ኢዮብ 27:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥ አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሲያስወግደው፣ ነፍሱንም ሲወስድበት ዐመፀኛ ምን ተስፋ አለው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ከሥጋቸው በመለየት ዕድሜአቸውን ባሳጠረ ጊዜ፥ እግዚአብሔርን የሚክዱ ሰዎች ምን ተስፋ ይኖራቸዋል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኀጢአተኛ ድኅነትን ተስፋ ያደርግ ዘንድ ለምን ደጅ ይጠናል? በእግዚአብሔርስ የማያምን ይድናልን? እንጃ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ የዝንጉ ሰው ተስፋው ምንድር ነው? |
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።