ኢዮብ 27:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥ አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤ አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቶ ክፉ ቃል ከአፌ አይወጣም፤ በአንደበቴም ሐሰት አልናገርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደበቴ ዐመፅን አይናገርም፤ ነፍሴም የዐመፅ አሳብን አትማርም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንፈሬ ኃጢአትን አትናገርም፥ አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም። |
ነገር ግን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል ኖሮ እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንሁ ነበር፤ ዳሩ ግን አውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።