ኢዮብ 24:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፥ ይሄዳሉ፥ ይጠወልጋሉም፥ እንደ ሌሎች ሁሉ ይከማቻሉ፥ እንደ እሸትም ራስ ይቈረጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሆኖም ይጠፋሉ፤ ዝቅ ዝቅ ብለው፤ እንደ ሌሎቹ ይከማቻሉ። እንደ እህል ራስም ይታጨዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ይበለጽጋሉ፤ ነገር ግን ወዲያውኑ እንደ አረም ጠውልገው ይጠፋሉ፤ እንደ እህልም ይታጨዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፥ ይሄዳሉ፥ ይጠወልጋሉም፥ እንደ ሌሎች ሁሉ ይከማቻሉ፥ እንደ እሸትም ራስ ይቈረጣሉ። |