ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
ኢዮብ 21:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ፦ የከበርቴው ቤት የት ነው? ክፉዎች ያደሩበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ፣ ‘የትልቁ ሰው ቤት፣ ኀጢአተኛውም የኖረበት ድንኳን የት አለ?’ አላችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ‘የዚያ የትልቅ ሰው ቤት የት ነው?’ የክፉውስ ሰው መኖሪያ የት ነው? ትላላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ፦ የአለቃው ቤት የት ነው? ኀጢአተኛውም ያደረበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ፦ የከበርቴው ቤት የት ነው? ኃጢአተኛውም ያደረበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋል። |
ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
እኔ እልከዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ወደሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፤ በቤታቸውም ውስጥ ይኖራል፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።”