ቁጣውንም አነደደብኝ፥ እንደ ጠላቱም ቈጠረኝ።
ቍጣው በላዬ ነድዷል፤ እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል።
እግዚአብሔር ተቈጥቶ መዓቱን አፈሰሰብኝ፤ እንደ ጠላትም ቈጠረኝ።
በታላቅ ቍጣም ያዘኝ እንደ ጠላትም ቈጠረኝ።
ቍጣውንም አነደደብኝ፥ እንደ ጠላቱም ቈጠረኝ።
ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ለምንድነው?
መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል።
በቁጣው ቆራረጠኝ፥ እርሱም ጠላኝ፥ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፥ ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፥
እነሆ፥ ሊወቅሰኝ ምክንያት ይፈጥራል፥ እንደ ጠላቱም ይቈጥረኛል፥
ዕድሜውንም አሳጠርህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው።
እኛ በቁጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና።
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።
ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ።
እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’”