ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘለዓለም በደለኛ እኔ ልሁን።
ኢዮብ 17:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እባክህን፥ አንተ ዋስ ሁነኝ፥ ለእኔ ተያዥ የሚሆነኝ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላክ ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ከአንተ በቀር ለእኔ የሚቆምልኝ የለምና አንተው ራስህ ተያዥ ሁነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ ጋር አጋና የሚማታ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም አንተ መያዣ ሆነህ ተዋሰኝ፥ ከእኔ ጋር አጋና የሚመታ ማን ነው? |
ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘለዓለም በደለኛ እኔ ልሁን።
እኔ አገልጋይ፥ ‘ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር፥ ለዘለዓለም በደለኛ አድርገህ ቁጠረኝ’ በማለት፥ ስለ ልጁ ደኅንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ።
እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጉረመረምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ላይ በማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።