ኢዮብ 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፥ ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተስፋ የማደርገው ቤት መቃብር ብቻ ከሆነ፣ መኝታዬንም በጨለማ ካነጠፍሁ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ የሚኖረኝ ዕድል ፈንታ ወደ ሙታን ዓለም መውረድ ነው፤ እዚያም በጨለማ አልጋዬን እዘረጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዘገይም ሲኦል ቤቴ ናት፤ ምንጣፌም በጨለማ ተነጥፎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፥ ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ። |
ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥