ኢዮብ 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ፈሪሃ እግዚአብሔርን እስከ መተው ደርሰሃል፥ በእግዚአብሔርም ፊት አምልኮን ታስቀራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን ንጽሕናን ታጣጥላለህ፤ በእግዚአብሔር ፊት የሆነ ጽሞናን ትከለክላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ እግዚአብሔርን መፍራት ትተሃል፤ ለእግዚአብሔር የሚገባውንም አምልኮ ታደናቅፋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ እግዚአብሔርን መፍራት ትተሃልን? በእግዚአብሔርስ ፊት እንዲህ ያለውን ቃል ትናገራለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም እግዚአብሔርን መፍራት ታፈርሳለህ፥ በእግዚአብሔር ፊት አምልኮን ታስቀራለህ። |
በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዓመፁ።
የሞተውን ሰው የሚያቃጥለው ዘመዱ አጥንቱን ከቤቱ አንስቶት ባወጣው ጊዜ፥ በቤቱም በውስጠኛው ክፍል ያለውን፦ “በእዚያ እስከ አሁን ድረስ ከአንተ ጋር ሰው አለን?” ይለዋል፥ እርሱም፦ “ማንም የለም” ይላል፤ ያንጊዜ፦ “የጌታን ስም ልንጠራ አይገባንምና ዝም በል” ይለዋል።