ኢዮብ 15:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአምላክ አልባ ሰው ጉባኤ ፍሬ የለውም፥ የጉቦ ድንኳኖችንም እሳት ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዐመፀኞች ጉባኤ ትመክናለች፤ የጉቦ ሱሰኞችም ድንኳን በእሳት ትበላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔርን ሕልውና የሚክዱ ሰዎች ዘር አይወጣላቸውም፤ በጉቦ የተሠሩ ቤቶችም በእሳት ይጋያሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኃጥኣን ሁሉ ሞት ምስክራቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀባዮችን ቤት ይበላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥ የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች። |
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”