ኢዮብ 13:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥ መንገዴንም ሁሉ ተቆጣጥረሃል፥ የእግሬንም ዱካ ወስነሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግሬን በእግር ግንድ ታጣብቃለህ፤ ውስጥ እግሬም ላይ ምልክት አድርገህ፣ ዱካዬን አጥብቀህ ትከታተላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮቼን በግንዶች መካከል አስረሃል፤ እያንዳንዱን እርምጃዬን ትቈጣጠራለህ፤ የእግሬን ዱካ ትመረምራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮችንም በድጥ አሰነካከልህ፥ ሥራዬንም ሁሉ መርምረሃል፤ እግሬም በቆመች ጊዜ ተውኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥ መንገዴንም ሁሉ መርምረሃል፥ የእግሬን ፍለጋ ወስነሃል። |