ኢዮብ 12:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፥ በእርሱ ዘንድ ምክርና ማስተዋል አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጥበብና ኀይል የእግዚአብሔር ናቸው፤ ምክርና ማስተዋልም በርሱ ዘንድ ይገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን ጥበብና ኀይል አለው፤ ምክርና አስተዋይነት የሚገኙት ከእርሱ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኀይል አለ፤ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፥ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው። |
እርሱ ግን ደግሞ ጠቢብ ነው፥ ክፉንም ነገር ያመጣል፥ ቃሉንም አይመልስም፥ በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።