ኢዮብ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ የሥጋ ዐይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ዐይንህ የሥጋ ለባሽ ዐይን ነውን? ሟች የሆነ የሰው ልጅ እንደሚያይ ታያለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ ዐይን እንደ ሰው ዐይን ነውን? ወይስ የምታየው እንደ ሰው ነውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ የሰው ዐይን አለህን? ወይስ መዋቲ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ የሥጋ ዓይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን? |
እንዲህም አላቸው “ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሰት ነውና።
ጌታ ግን ሳሙኤልን፥ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። ጌታ የሚያየው፥ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ ጌታ ግን ልብን ያያል” አለው።