ኤርምያስ 6:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ሁሉ እጅግ ዓመፀኞች ናቸው፤ በጠማማነት ይሄዳሉ፤ ናስና ብረት ናቸው፤ ሁሉ ርኩሰትን ያደርጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም ለማማት የሚዞሩ፣ ድድር ዐመፀኞች፣ ናስና ብረት የሆኑ፣ ምግባረ ብልሹዎች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም እንደ ነሐስና እንደ ብረት የጠነከሩ፤ በእልህም የተወጠሩ ዐመፀኞች ናቸው። ሁሉም የተበላሹ የሐሜት ሱሰኞች ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ሁሉ እጅግ ደንቆሮዎች ናቸው፤ በጠማማነት ይሄዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ሁሉ እጅግ ዓመፀኞች ናቸው፥ በጠማማነት ይሄዳሉ፥ ናስና ብረት ናቸው፥ ሁሉ ርኵሰትን ያደርጋሉ። |
እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።
የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።
ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።
በርኩሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ መዓቴን በአንቺ ላይ እስክጨርስ ድረስ ከእንግዲህ ወዲያ ከርኩሰትሽ ንፁህ አትሆኚም ምክንያቱም አነጻሁሽ ነገር ግን ንፁህ አልሆንሺምና።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቁጣህም መጣ፤ በሙታንም የምትፈርድበት ዘመን መጣ፤ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን፥ ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን የምትሰጥበት ምድርንም የሚያጠፉትን የምታጠፋበት ዘመን መጣ።”