ኤርምያስ 52:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡከደነፆር ማርኮ ያፈለሰው የሕዝብ ቍጥር ብዛት ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰደው ሕዝብ ቍጥር እንደሚከተለው ነው፦ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፣ ሦስት ሺሕ ሃያ ሦስት አይሁድ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ብዛት ማስታወሻ ይህ ነው፤ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ የማረካቸው ሦስት ሺህ ኻያ ሦስት አይሁድ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይሁድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፥ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፥ |
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።