ኤርምያስ 51:61 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፦ “ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ልብ ብለህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፤ “ባቢሎን በደረስህ ጊዜ፣ ይህን ቃል ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማንበብ አትዘንጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራያንም እንዲህ አልኩት “ባቢሎን እንደ ደረስህ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ለሕዝቡ አንብብላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፥ “ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ እይ፤ ይህንም ቃል ሁሉ አንብብና፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፦ ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ እይ፥ ይህንም ቃል ሁሉ አንብብና፦ |
እንዲህ በል፦ ‘አቤቱ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ልታጠፋት በዚህች ስፍራ ላይ አንተ ተናግረሃል።’
ይህም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበ በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንዲነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምታገኙትን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።