Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ቈላስይስ 4:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ይህም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበ በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንዲነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምታገኙትን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ይህች መልእክት ከተነበበችላችሁ በኋላ በሎዶቅያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ደግሞ በሎዶቅያ ያለችውን መልእክት አንብቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህችን መልእክት እናንተ ካነበባችኋት በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይህ​ችን መል​እ​ክት እና​ንተ አን​ብ​ባ​ችሁ፥ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ያነ​ብ​ቡ​አት ዘንድ ወደ ሎዶ​ቅያ ላኩ​አት፤ ዳግ​መ​ኛም እና​ንተ ከሎ​ዶ​ቅያ የጻ​ፍ​ኋ​ትን መል​እ​ክት አን​ብ​ቡ​አት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።

Ver Capítulo Copiar




ቈላስይስ 4:16
6 Referencias Cruzadas  

ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፦ “ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ልብ ብለህ ይህን ቃል ሁሉ አንብብና፥


ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም አይተውት ስለማያውቁት ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል እንደምጋደል እንድታውቁ እወዳለሁና፤


ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ በሥራ እንደደከመ እመሰክርለታለሁና።


በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤትዋም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።


ይህ መልእክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ ዐደራ እላችኋለሁ።


በዚህ መልእክት በኩል ለተላከው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ሰው በምልክት ለዩት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos