ኤርምያስ 50:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ቁጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይሣቀቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ፣ የሚኖርባት አይገኝም፤ በቍስሎቿም ሁሉ ምክንያት፣ በባቢሎን የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ ያፌዝባታልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቊጣዬ የተነሣ በባቢሎን መኖር የሚችል የለም፤ ፈራርሳ ትቀራለች፤ በአጠገብዋ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ ይደነግጣልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፥ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል። |
ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።
እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ወደዚህችም ከተማ እመልሳቸዋለሁ፤ እርሷንም ይወጋሉ ይይዙአታልም በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
ሕዝብ ከሰሜን በእርሷ ላይ ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፥ የሚቀመጥባትም አይገኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሸሽተው ሄደዋል።
እንዲህ በል፦ ‘አቤቱ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ልታጠፋት በዚህች ስፍራ ላይ አንተ ተናግረሃል።’
ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።
“የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና ጌታ ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ።