እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።
ኤርምያስ 44:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድሪቱም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን ጌታ አያስታውሰውምን? በልቡስ አያኖረውምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁና ባለሥልጣኖቻችሁ እንዲሁም የምድሪቱ ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ያጠናችሁትን እግዚአብሔር የማያስታውሰውና የዘነጋው ይመስላችኋልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተና የቀድሞ አባቶቻችሁ፥ ንጉሦቻችሁና መሪዎቻችሁ፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ዕጣን ታጥኑ እንደ ነበረ፥ እግዚአብሔር አያስበውም ወይም ረስቶታል ብላችሁ ታስባላችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተና አባቶቻችሁ፥ ነገሥታቶቻችሁም፥ አለቆቻችሁም የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው፥ በልቡም ያኖረው አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው በልቡም ያኖረው አይደለምን? |
እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።
ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለአሳፋሪ ነገር መሠዊያዎችን ሠርታችኋል፥ እነርሱም ለበዓል የምታጥኑባቸው መሠዊያዎች ናቸው።
ጌታ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “በእውነት መቅበዝበዝን ወድደዋል፥ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ ጌታ በእነርሱ ደስ አይሰኝም፥ በደላቸውንም አሁን ያስታውሳል ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።”
ይህንንም የማደርገው እኔን ለማስቈጣት፥ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፥ አለቆቻቸውና ካህናቶቻቸው፥ ነብዮቻቸውና የይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ፥ ስላደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።
ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ እንዳደረግነው፥ ለሰማይ ንግሥት ለማጠን የመጠጥንም ቁርባን ለእርሷ ለማፍሰስ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፤ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።
በውኑ በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፥ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፥ የሚስቶቻቸውንም ክፋት፥ የእናንተንም ክፋት፥ የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን?
ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንም ሴቱንም፥ ልጁንም ሕፃኑንም፥ የቀንድ ከብቱንም በጉንም፥ ግመሉንም አህያውንም ግደል።’ ”