Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 16:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ለራስሽ ጉብታን ሠራሽ፥ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታን ለራስሽ አዘጋጀሽ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ለራስሽ ጕብታን አበጀሽ፤ በየአደባባዩም የማምለኪያ ኰረብታ ሠራሽ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 መድረክ እየሠራሽ በየ አደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ አዘጋጀሽ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የም​ት​ሰ​ስ​ኝ​በ​ትን ቤት ለራ​ስሽ ሠራሽ፤ በአ​ደ​ባ​ባዩ ሁሉ ከፍ ያለ ቦታን አደ​ረ​ግሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ከክፋትሽም ሁሉ በኋላ የምንዝርናን ስፍራ፥ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታን ለራስሽ ሠራሽ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 16:24
19 Referencias Cruzadas  

በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ ጉብታሽን ያፈርሳሉ፥ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፤ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፥ የሚያምሩ ጌጣጌጦችሽን ይወስዳሉ፥ ዕርቃንሽንና ዕራቁትሽን ይተዉሻል።


በየመንገዱ ራስ የምንዝርናሽን ስፍራ ሠርተሻል በየአደባባዩም ከፍ ያለውን ቦታሽን አድርገሻል። ዋጋዋን እንደምትንቅ እንደ ጋለሞታ አልሆንሽም።


“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።


ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፥ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ።


በኰረብታ መስገጃዎቻቸውም አስቈጡት፥ በተቀረጹ ምስሎቻቸውም አስቀኑት።


ወደ ተራቈቱ ኮረብቶች አይኖችሽን አንሺ፥ ተመልከቺም፤ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ልክ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አረባዊ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸዋለሽ፤ በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።


በሜዳ ያለው ተራራዬ ሆይ! ባለጠግነትህንና መዝገቦችህን ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችህም ስለ ኃጢአት በድንበሮችህ ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ።


እናንተ በባሉጥ ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፥ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?


የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።


ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤


ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለአሳፋሪ ነገር መሠዊያዎችን ሠርታችኋል፥ እነርሱም ለበዓል የምታጥኑባቸው መሠዊያዎች ናቸው።


ከዚህ ሁሉ ክፋትሽ በኋላ ወዮ! ወዮልሽ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤


ዳግምም በይሁዳ ተራሮች ላይ በከፍታ ላይ የሚገኙ የማምለኪያ ሥፍራዎችን ሠራ፥ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን እንዲያመነዝሩ አደረጋቸው፥ ይሁዳንም አሳተው።


በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት ለማጠን የኮረብታ መስገጃዎች አሠራ የአባቶቹንም አምላክ ጌታን አስቈጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios