እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፥ የብረት መቆፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
ኤርምያስ 43:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ትላልቅ ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፥ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ በፈርዖን ቤት መግቢያ ባለው በቅጥራኑና በጡቡ ደጃፍ ሸሽጋቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ትልልቅ ድንጋዮች ውሰድና በጣፍናስ ባለው የፈርዖን ቤተ መንግሥት በር ላይ የይሁዳ ሰዎች እያዩ በሸክላ ጡብ ወለል ውስጥ ቅበራቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጥቂት ታላላቅ ድንጋዮች ፈልገህ ካገኘህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች ጥቂቱ እያዩህ በከተማይቱ ቤተ መንግሥት መግቢያ ፊት ለፊት ባለው ከሲሚንቶ በተሠራው ወለል ሥር ቅበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፥ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፥ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው፥ |
እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፥ የብረት መቆፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
እንዲህም በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ልኬ ባርያዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አመጣለሁ፥ ዙፋኑንም እኔ በሸሸግኋቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም የዙፋኑን ድንኳን በላያቸው ይዘረጋል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለሚሻው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፥ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚሽዋት እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።”
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ ወስዶ የገዛ እጁንና እግሩን አስሮ “እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ ‘ይህ መታጠቂያ ያለውን ሰው አይሁድ በኢየሩሳሌም እንደዚህ ያስሩታል፤ በአሕዛብም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል፤’ ይላል፤” አለ።
አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።