ኤርምያስ 42:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም አሁን ሄዳችሁ ለመቀመጥ በወደዳችሁበት በዚያ ስፍራ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንደምትሞቱ በእርግጥ እወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በርግጥ ዕወቁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አሁን ሄዳችሁ ልትኖሩ በምትፈልጉበት ቦታ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንደምትሞቱ እርግጠኞች ሁኑ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ ዕወቁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ሄዳችሁ እንድትቀመጡ በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ። |
ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታሉ፤ እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ከእነርሱ አንድም ሰው በሕይወት አይተርፍም፥ አንድም ሰው አያመልጥም።
ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ትሩፍ እወስዳለሁ፥ ሁሉም ይጠፋሉ፥ በግብጽም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በፍርስራሽ ስፍራዎች ያሉት በሰይፍ ይወድቃሉ፥ በሜዳ ያሉትን መብል እንዲሆን ለአራዊት እሰጠዋለሁ፥ በምሽጎችና በዋሻዎች ያሉት በቸነፈር ይሞታሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእጅህ አጨብጭብ፥ በእግርህም እየረገጥህ፥ ስለ የእስራኤል ቤት ክፉ የርኩሰት ሥራዎቻቸው ሁሉ ወዮ! በል፤ በሰይፍ፥ በራብና በቸነፈር ይወድቃሉና፤
በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፥ በቅርብ ያለውም በሰይፍ ይወድቃል፥ በሕይወት የተረፈውና የዳነውም በራብ ይሞታል፥ መዓቴን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።
እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።