ሕዝቅኤል 33:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በፍርስራሽ ስፍራዎች ያሉት በሰይፍ ይወድቃሉ፥ በሜዳ ያሉትን መብል እንዲሆን ለአራዊት እሰጠዋለሁ፥ በምሽጎችና በዋሻዎች ያሉት በቸነፈር ይሞታሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 “እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፍርስራሾች ውስጥ የተረፉት በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በገጠር ያሉትን ቦጫጭቀው እንዲበሏቸው ለዱር አራዊት እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽግና በዋሻ ያሉትም በቸነፈር ይሞታሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 “እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በፈራረሱ ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ በእርግጥ ይገደላሉ ብዬ ያስጠነቀቅኋቸው መሆኑን ገልጠህ ንገራቸው፤ በገጠር የሚኖሩ የአራዊት ምግብ ይሆናሉ፤ በየተራራውና በየዋሻው ተደብቀው ያሉትም በመቅሠፍት ያልቃሉ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባድማ ስፍራዎች ያሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በምድረ በዳ ያለውን ለአራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ፤ በአምባዎችና በዋሻዎች ያሉ በቸነፈር ይሞታሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባድማ ስፍራዎች ያሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ በምድረ በዳ ያለውን ለአራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ፥ በአምባዎችና በዋሾች ያሉ በቸነፈር ይሞታሉ። Ver Capítulo |