ኤርምያስ 25:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእረኞችም የመሸሻ ስፍራ ከመንጋ አውራዎችም ማምለጫ ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞች የሚሸሹበት፣ የመንጋ ጠባቂዎችም የሚያመልጡበት የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎቹ መሸሻ የላቸውም፤ የሕዝቡም ጠባቂዎች ማምለጥ አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእረኞች የማይጠፋ የለም፤ የበጎች አውራዎችም አይድኑም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽሽትም ከእረኞች ማምለጥም ከመንጋ አውራዎች ይጠፋል። |
የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ፊት ለፊትም ያነጋግረዋል፥ ዓይኑም ዓይኑን ያያል እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤
አንተም በእርግጥ ትያዛለህ ለእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፤ ዓይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፥ እርሱም ከአንተ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራል፥ ወደ ባቢሎንም ትሄዳለህ።’
ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ “በውኑ ከጌታ ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ “አዎን አለ” ብሎ መለሰ። ከዚያም በኋላ፦ “በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አለ።
ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”
በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ከአስፈሪውም ነገር የሸሸ በጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም ውስጥ የሚወጣ በወጥመድ ይያዛል።
ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?