ሕዝቅኤል 17:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ንጉሡ ግን በርሱ ላይ ዐመፀ፤ ፈረሶችና ብዙ ሰራዊት ለማግኘት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ይሳካለት ይሆን? እንዲህ ዐይነቱን ነገር የፈጸመ ያመልጣልን? ውል ያፈረሰስ ሳይቀጣ ይቀራልን? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ነገር ግን የይሁዳ ንጉሥ ዐምፆ ፈረሶችንና ታላቅ ሠራዊት እንዲያመጡለት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ታዲያ ይህ ዕቅዱ ይሳካለታልን? በዚህስ ሊያመልጥ ይችላልን? ውሉን የሚያፈርስ ከሆነ ከቅጣት ከቶ ያመልጣልን? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ ያፈረሰ ያመልጣልን? Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ አፍርሶ ያመልጣልን? Ver Capítulo |