ኤርምያስ 25:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ቡዝንም፥ የጠጉራቸውንም ማዕዘን የሚቈርጡትን ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድዳንን፣ ቴማንን፣ ቡዝን፣ ጠጕራቸውን ዙሪያውን የሚከረከሙትን ሕዝብ ሁሉ፣ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ሮስንም፥ ፊታቸውን የሚከተቡትን ሁሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ቡዝንም፥ ጠጕራቸውንም የሚቈርጡትን ሁሉ፥ |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ የእንስሶቻቸውም ብዛት ይማረካል፤ ጠጉራቸውንም ዙሪያውን የተላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከሁሉም አቅጣጫ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ።
የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምጐበኝበት ጊዜ አመጣበታለሁና፥ እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! ሽሹ፥ ወደ ኋላ ተመለሱ፥ በጥልቅም ውስጥ ተቀመጡ።
እንዲሁም የእስራኤል ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና፥ አሕዛብም ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና ግብጽንና ይሁዳን፥ ኤዶምያስንም፥ የአሞንንም ልጆች፥ ሞአብንም፥ በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጉራቸውን በዙሪያ የተላጩትን ሁሉ በዚያን ዘመን እቀጣለሁ።”
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።