ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
ኤርምያስ 21:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን የጦር መሣርያ እመልሳለሁ፥ እነርሱንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከቅጥሩ ውጭ የከበቧችሁን የባቢሎንን ንጉሥና ባቢሎናውያንን ለመውጋት በእጃችሁ የያዛችሁትን የጦር መሣሪያ በእናንተው ላይ አዞራለሁ፤ ወደዚህችም ከተማ ሰብስቤ አስገባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፤ ‘ሴዴቅያስ ሆ! ከቅጽርህ በስተውጪ በኩል ከበባ ያደረጉብህን የባቢሎንን ንጉሥና ባቢሎናውያንን የምትዋጋበት የጦር መሣሪያ አንተን ተመልሶ እንዲያጠቃ አደርጋለሁ፤ የጦር መሣሪያውንም በከተማይቱ መካከል እንዲከመር አደርጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን የጦር መሣሪያችሁን እሰጣችኋለሁ፤ እነዚያንም በዚህች ከተማ መካከል እሰበስባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የባቢሎንን ንጉሥ በቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ፥ እነዚያንም ወደዚህች ከተማ ውስጥ እሰበስባቸዋለሁ። |
ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።
ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ ዐይኖችህም ያያሉ፤ ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እርሱም ወደ ባቢሎን ያፈልሳቸዋል በሰይፍም ይገድላቸዋል።
እነሆ፥ አፈር ደልድለው የመሸጉ፥ ከተማይቱን ሊይዙአት ቀርበዋል፤ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፤ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንዲህ ብሎ አሳስሮት ነበርና፦ “ስለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ እርሱም ይይዛታል፤
እርሱም ሴዴቅያስን ወደ ባቢሎን ያፈልሰዋል፥ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፥ ይላል ጌታ፤ ከከላዳውያን ጋር ብትዋጉ ምንም አይቀናችሁም’?”
ከለዳውያን ጋር ለመዋጋት ወጥተዋል፤ ነገር ግን በቁጣዬና በመዓቴ በገደልኋቸው ሰዎች ሬሳዎች ሊሞሉአቸው ነው፥ ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ ሰውሬአለሁና።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሆነ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና በእነርሱ ላይ የተናገርኩትን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በተቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋር ናቦ፥ የራፌሱ ሠርሰኪም፥ የራብማጉ ኤርጌል ሳራስር፥ ከተረፉት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።
ጋሜል። በጽኑ ቁጣው የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ ቀጠቀጠ፥ ቀኝ እጁን ከጠላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያውም እንደሚባላ እንደ እሳት ነበልባል ያዕቆብን አቃጠለ።
ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ።
አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እንዲነሱ እሰበስባቸዋለሁ፤ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማይቱም እኩሌታ ለምርኮ ይጋዛል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዋ አይፈናቃልም።