La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ፦ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል” ብለህ ይህን ቃል ትነግራቸዋለህ፤ እነርሱም፦ “ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንደሚሞላ በእርግጥ እኛ አናውቅምን?” ይሉሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እንዲህ በላቸው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል’፤ እነርሱም፣ ‘ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ አናውቅምን?’ ቢሉህ፣

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “ኤርምያስ ሆይ! ‘እያንዳንዱ ማድጋ በወይን ጠጅ የተሞላ ይሆናል’ ብለህ ለእስራኤል ሕዝብ ንገር፤ በዚያን ጊዜ እነርሱ ‘ማድጋ በወይን ጠጅ መሞላቱን የማናውቅ ይመስልሃልን?’ ይሉሃል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ማድጋ ሁሉ የወ​ይን ጠጅ ይሞ​ላል” ብለህ ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ማድጋ ሁሉ የወ​ይን ጠጅ እን​ዲ​ሞላ በውኑ እኛ አና​ው​ቅ​ምን?” ቢሉህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል ብለህ ትነግራቸዋለህ፥ እነርሱም፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን? ይሉሃል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 13:12
4 Referencias Cruzadas  

መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፥ እንዲሁ ሕዝብና ስም፥ ምስጋናና ክብር እንዲሆኑልኝ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ነገር ግን አልሰሙም።”


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት ካህናቱንም ነቢያቱንም በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።


በመካከላቸውም ከምልከው ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ ይወላገዳሉም ያብዳሉም።”


ሕዝቡም፦ “እነዚህ የምታደርጋቸውው ነገሮች ለእኛ ምን እንደሆነ አትነግረንምን?” አሉኝ።