እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
ኤርምያስ 11:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚተርፍ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚቀጡበት ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ መዓት ስለማመጣ፣ ከእነርሱ የሚተርፍ አንድም አይኖርም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐናቶት ሕዝብ ላይ መቅሠፍት የማመጣበት ዘመን ሲደርስ ከእነርሱ መካከል አንድ ሰው እንኳ አይተርፍም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚተርፍ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም። |
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ፤ እነርሱም፦ “ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፥ ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታወስ ከሕያዋን ምድር እናስወግደው” ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች እንደ ምታዳልጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች፥ እነርሱም ወደ እርሷ ይገፈተራሉ ተፍገምግመውም ይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥ ይላል ጌታ።
እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እመለከታለሁ፤ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።
በእርሷም መካከል ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮችዋ እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የመጐብኘታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፥ በአንድነትም ሸሹ፥ አልቆሙምም።
በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ከአስፈሪውም ነገር የሸሸ በጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም ውስጥ የሚወጣ በወጥመድ ይያዛል።
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የተረፉትን ፈጽሞ ይለቅሙአችኋል፤ እጅህንም እንደ ለቃሚ በቅርንጫፎቹ ላይ ዳግመኛ ዘርጋ።”
አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።”
የበቀል ወራት መጥቷል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ይወቀው፤ ከበደልህና ከጥላቻህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሞኝ ሆኗል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።
ጌታ ተናግሮአልና የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባልም፥ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናሉ፥ እነርሱንም ያቃጥሉአቸዋል ይበሉአቸውማል፥ ከዔሳውም ቤት የሚተርፍ አይኖርም።
ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።
አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን በምድር ላይ ይጨፈልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም በድንጋይ ላይ የሚኖር ድንጋይ አያስቀሩም፤ የተጐብኘሽበትን ዘመን አላወቅሽምና።”