ኤርምያስ 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ሄደው ይጮኻሉ፤ እነርሱ ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ ሊረዷቸው አይችሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ መሥዋዕት ወደሚያቀርቡላቸው ባዕዳን አማልክት ሄደው ርዳታ እንዲያደርጉላቸው ይጮኻሉ፤ ነገር ግን እነርሱ ይህ ጥፋት በሚመጣበት ጊዜ ሊያድኑአቸው አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው፥ በመከራቸው ጊዜ ከቶ ወደማያድኗቸው አማልክት ይጮኻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው አማልክት ይጮኻሉ፥ ነገር ግን በመከራቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም። |
እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፥ በዚያም ይቆማል፤ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል ለከንቱ ነገርም ዐጥነዋል፤ ከመንገዳቸውም አሰናክለዋቸዋል ከቀድሞውም ጐዳና ርቀው ወዳልተሠራው ወደ ጠማማው መንገድ ሄደዋል።
ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።
እናንተም እንድትጠፉ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ እንድትሆኑ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት አጥናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
እነዚያ የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥ የመጠጥ መለማመኛቸውንም ወይን የጠጡ? እስቲ እነርሱ ይነሡና ይርዱአችሁ! እስቲ መጠጊያም ይሁኑላችሁ!’”