ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።
ኢሳይያስ 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ አሕዛብ፤ ፎክሩ፤ ግን ደንግጡ። በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ፤ ነገር ግን ደንግጡ! በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ። ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ አሕዛብ ጦርነትን ዐወጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ እናንተም የሩቅ አገር ሰዎች ሁሉ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ አሁንም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሆይ፥ ዕወቁና ደንግጡ፤ እስከ ምድር ዳርቻም ስሙ፤ ኀያላን! ድል ሁኑ፤ ዳግመኛም ብትበረቱ እንደ ገና ድል ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ ሆይ፥ ዕወቁና ደንግጡ፥ እናንተም ምድራችሁ የራቀ ሁሉ፥ አድምጡ፥ ታጠቁ፥ ደንግጡ፥ ታጠቁ፥ ደንግጡ። |
ንጉሥ አክዓብ መልእክተኞቹን “እውነተኛ ወታደር መደንፋት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም ብላችሁ ለንጉሥ ቤንሀዳድ ንገሩት” ሲል መለሰላቸው።
ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፥ እንዲሰበሩም፥ በወጥመድም እንዲያዙ፥ የጌታ ቃል በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፥ በደንብ ላይ ደንብ፥ በደንብ ላይ ደንብ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።
ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርሷም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።