Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 8:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ፤ ነገር ግን ደንግጡ! በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ። ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እናንተ አሕዛብ፤ ፎክሩ፤ ግን ደንግጡ። በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተ አሕዛብ ጦርነትን ዐወጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ እናንተም የሩቅ አገር ሰዎች ሁሉ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ! ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ፤ አሁንም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ትደመሰሳላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አሕ​ዛብ ሆይ፥ ዕወ​ቁና ደን​ግጡ፤ እስከ ምድር ዳር​ቻም ስሙ፤ ኀያ​ላን! ድል ሁኑ፤ ዳግ​መ​ኛም ብት​በ​ረቱ እንደ ገና ድል ትሆ​ና​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አሕዛብ ሆይ፥ ዕወቁና ደንግጡ፥ እናንተም ምድራችሁ የራቀ ሁሉ፥ አድምጡ፥ ታጠቁ፥ ደንግጡ፥ ታጠቁ፥ ደንግጡ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 8:9
24 Referencias Cruzadas  

የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ ‘ታጥቆ ለጦርነት የሚወጣ ሰው የጦር ትጥቁን እንደ ፈታ ሰው መደንፋት የለበትም’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው።


ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።


ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፣ በትእዛዝ ላይ ትእዛዝ፤ በደንብ ላይ ደንብ፣ በደንብ ላይ ደንብ፤ እዚህ ጥቂት እዚያ ጥቂት ይሆንባቸዋል። ይህ የሚሆንባቸው ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲቈስሉና በወጥመድ እንዲያዙ፣ እንዲማረኩም ነው።


ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።


ማንም ጕዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ ጕዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።


አሁን የሚያስፈራችሁን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋራ ነኝና አትፍሩ ይላል እግዚአብሔር፤


“ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤ ለውጊያም ውጡ!


ፈረሶችን ጫኑ፤ በላያቸውም ተቀመጡ! የራስ ቍር ደፍታችሁ፣ በየቦታችሁ ቁሙ፤ ጦራችሁን ወልውሉ፤ ጥሩራችሁን ልበሱ!


“አንቺ የእኔ ቈመጥ፣ የጦር መሣሪያዬ ነሽ፤ በአንቺ ሕዝቦችን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ መንግሥታትን አጠፋለሁ፤


“ ‘አንተና በዙሪያህ የተሰበሰቡት ሁሉ ተነሡ፤ ተዘጋጁ፤ አንተም መሪያቸው ሁን።


ከብዙ ቀን በኋላ ለጦርነት ትጠራለህ። በኋለኛው ዘመንም ከጦርነት ያገገመችውን፣ ሕዝቧ ከአያሌ አሕዛብ መካከል ወጥቶ የተሰበሰበውን፣ ለብዙ ጊዜ ባድማ በነበረው በእስራኤል ተራሮች ላይ የሰፈረውን ወገን ትወርራለህ። ከሕዝቦች መካከል ወጥተው፣ አሁን ሁሉም ያለ ሥጋት ይኖራሉ።


እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኀይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በአንድነት ሰፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos