ኢሳይያስ 63:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዘለዓለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ እኮ ጥንትም የአንተው ነን፤ እነርሱን ግን አንተ አላገዝሃቸውም፤ በስምህም አልተጠሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በአንተ እንዳልተገዙና በስምህ እንዳልተጠሩ ወገኖች ከሆንን ብዙ ጊዜአችን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥንት እንዳልገዛኸን ስምህም በእኛ ላይ እንዳልተጠራ ሆነናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዘላለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል። |
ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።
ግራ እንደ ተጋባ ሰው፥ ለማዳንም እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ! በመካከላችን ነህ፥ እኛም በስምህ ተጠርተናል፤ አትተወን።”
በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።
አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።