ኢሳይያስ 60:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጽግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ታያለሽ፤ ታብረቀርቂአለሽ፤ ልብሽ ይዘልላል፤ በደስታም ይሞላል። በባሕሮች ያለው ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል፤ የነገሥታትም ብልጽግና የአንቺ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜ አይተሽ ትፈሪያለሽ፤ የአሕዛብና የሀገሮች ብልጽግና ወደ አንቺ ይመለሳልና፥ ልብሽ ይደነግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል። |
ንግድዋና ዋጋው ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል፤ ንግድዋንም በልተው ይጠግቡ ዘንድ ማለፊያም ልብስ ይለብሱ ዘንድ በጌታ ፊት ለሚኖሩ ይሆናል እንጂ በዕቃ ቤትና በግምጃ ቤት ውስጥ አይከተትም።
እናንተ ግን የጌታ ካህናት ትባላላችሁ፤ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፥ በሀብታቸውም ትከብራላችሁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆም፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፥ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጉልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሏችኋል።
የምሠራላቸውንም በጎነት ሁሉ በሚሰሙ የምድር አሕዛብ ሁሉ ፊት ይህች ከተማ ለእኔ የምስጋናና የክብር የደስታም ስም ትሆናለች፤ እኔም ስላደረግሁላት በጎነትና ሰላም ሁሉ ይፈራሉ ይንቀጠቀጣሉም።
ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።
እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከላከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”
ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥ ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።