Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 11:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ወንድሞች ሆይ፤ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ፣ ይህን ምስጢር ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል በድንዳኔ ውስጥ ዐልፋለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 11:25
41 Referencias Cruzadas  

በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉ ይሰደዳሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።


እንግዲህ በወንጌሌ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም ስብከት፥ ለዘመናት ተሰውሮ በነበረው የምሥጢር ግልፀት ሊያጸናችሁ ለሚችለው ለእርሱ፥


እርስ በርሳችሁ በአንድ ነገር ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፤ ነገር ግን የተናቁትን ቅረቡ። በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።


ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ለመንፋት የተዘጋጀው መልአክ የመለከቱን ድምፁም በሚያሰማባቸው ቀኖች፥ የእግዚአብሔር ምሥጢር ለባርያዎቹ ለነቢያት የምሥራች በሰበከላቸው መሠረት ይፈጸማል፤” አለ።


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሰዎች ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘለዓለም የተሰወረው የምሥጢር አሳብ ምን እንደሆነ ለሁሉ እንድገልጥ፥


ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፥ ጌታንም የሚሹት ያመሰግኑታል፥ ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይሁን።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”


ወዳጆች ሆይ! እናንተ ግን በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።


ወንድሞች ሆይ! ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ፤ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤


ወንድሞች ሆይ! በሌሎቹ ሕዝቦች እንዳገኘሁት በእናንተም ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳቀድሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።


ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።


ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፤ በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!


ስሙ ለዘለዓለም ይታወስ፥ እንደ ፀሐይ ዕድሜ ስሙ ጸንቶ ይኑር፥ የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረኩ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑት፥


ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ! አላዋቂ እንድትሆኑ አልፈልግም።


ሰነፍ ሰው በጥበብ ከሚመልሱ ከሰባት ሰዎች ይልቅ ለራሱ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።


ለራሱ ጠቢብ የሆነ የሚምስለውን ሰው አየኽውን? ከእርሱ ይልቅ ሞኝ ተስፋ አለው።


የዕርገት መዝሙር። ጌታ ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፥ ጌታ ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


ጠቢብ ማነው? ይህንን ይፈጽም፥ እርሱ የጌታንም ጽኑ ፍቅር ይገነዘባል።


እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ማምጣት ይገባኛል፤ ድምፄንም ይሰማሉ፤ አንድም መንጋ ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ።


እንግዲህ የፈለገውን ይምረዋል የፈለገውንም እልከኛ ያደርገዋል።


ነገር ግን በደላቸው ለዓለም ባለጠግነት ውድቀታቸውም ለአሕዛብ ባለጠግነት ከሆነ፥ ይልቁንስ መሙላታቸው እንዴት ይሆን?


አንተ በተፈጥሮ የበረሃ ከነበረ የወይራ ዛፍ ተቆርጠህ እንደ አፈጣጠርህ ሳትሆን በመልካም የወይራ ዛፍ ከገባህ፥ ይልቁንስ እነዚያ በተፈጥሮአቸው ቅርንጫፎች የሆኑት በራሳቸው የወይራ ዛፍ እንዴት አይገቡም?


ነገር ግን፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር ተሰውሮም የነበረውን እንናገራለን።


እንግዲህ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ አገልጋዮችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢራት መጋቢዎች ይቁጠረን።


በክርስቶስ ለማድረግ የወደደውን የአሳቡን፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናል፤


እነርሱ ባለማወቃቸውና በልባቸው ደንዳንነት ምክንያት፥ ልቡናቸው ጨለመ፤ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios